Fana: At a Speed of Life!

 ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 714 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል አርአያ ሆናለች- ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 714 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል አርአያ ሆናለች አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ በስኬት የተጠናቀቀውን የአንድ ጀንበር አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተፈጥሮ ሚዛንን ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አውስተዋል፡፡

አረንጓዴ ዐሻራ ተፈጥሮን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ የተከበረ ተግባር መሆኑን ጠቁመው÷ መርሐ ግብሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ ዛሬ ኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 714 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኞች በመትከል አርአያ መሆኗን በመመልከታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.