Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ከተማ በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ዛሬ ማለዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ዲቪዠን ኃላፊ ኮማንደር ከበደ ከኔራ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ አደጋው የደረሰው በክፍለ ከተማው ልዩ ቦታው ወንዶ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ሲኖትራክ የጭነት ተሸከርካሪ ከሀዋሳ ከተማ ወደ ቱላ ሲጓዝ በነበረበት ወቅት አነስተኛ የከተማ ታክሲ በመግጨት እንዲሁም እግረኞች ላይ በመውጣት የሞትና የአካል ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት።

በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ 2 ሰዎች ከባድ ጉዳት አንዲሁም 6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ህክምና ተቋም መወሰዳቸውን ገልጸው፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ነግረውናል፡፡

በደብሪቱ በዛብህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.