የመዲናዋ የኮሪደር ልማት የፈጠራ እና የፍጥነት ውጤት ማሣያ ነው – አቶ ሙስጠፋ መሐመድ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ የቀየረ የፈጠራ እና የፍጥነት ውጤት ማሣያ ነው አሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ከእንጦጦ እስከ 4 ኪሎ ፕላዛ፣ የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚቪሽንና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ ሙስጠፋ መሐመድ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፤ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ነው፡፡
የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚቢሽን የኢትዮጵያን መጻኢ ተስፋ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ልማት ለምታደርገው የለውጥ ጉዞ ታላቅ ምዕራፍ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የተመለከቷቸው የልማት ፕሮጀክቶች የፍጥነትና የፈጠራ ውጤቶች መሆናቸውን ጠቁመው፤ ከሥራ ፈጠራ እና ከሌሎችም አኳያ የህዝቡን ኑሮ የቀየሩ ናቸው ብለዋል።
በሀገር ደረጃ ተግባራዊ የተደረጉ ሁሉም ኢኒሼቲቮች በሶማሌ ክልል መጀመራቸውን ገልጸው፤ የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራዎች በቅርቡ እንደሚመረቁ መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በክልሉ የማደራጀት ስራዎች መጀመራቸውን ጠቁመው፤ የገጠር ኮሪደር፣ የሌማት ትሩፋት እንዲሁም በአረንጓዴ ዐሻራ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!