Fana: At a Speed of Life!

የእንጦጦ – 4 ኪሎ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችን እንዲያስተሳስር ተደርጎ ተገንብቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንጦጦ – 4 ኪሎ የኮሪደር ልማት ሌሎች የከተማዋን ፕሮጀክቶችን እንዲያስተሳስር ተደርጎ ተገንብቷል አሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበሩ (ዶ/ር)፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ከእንጦጦ እስከ 4 ኪሎ ፕላዛ ድረስ የተሰራውን የኮሪደር ልማት ጎብኝተዋል፡፡

ጀማሉ ጀንበሩ (ዶ/ር) በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት÷ በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ከተገነቡ ፕሮጀክቶች መካከል የእንጦጦ – 4 ኪሎ እና ጉለሌ እፅዋት ማዕከል የሚወስደው የኮሪደር ልማት ይገኙበታል።

የእንጦጦ – 4 ኪሎ ፕሮጀክት ቀደም ሲል ከተገነቡት የ4 ኪሎ-ፒያሳ እና የካሳንቺስ የኮሪደር ልማቶች እና ለወደፊትም ከሚገነቡ ፕሮጀክቶች ጋር ለማስተሳሰር ታቅዶ ተገነባ ነው ብለዋል።

የእንጦጦ – 4 ኪሎ የኮሪደር ልማት ከጫካ ፕሮጀክት፣ ከእንጦጦ ፓርክ እና ከጉለሌ እፅዋት ማዕከል ጋር የሚያስተሳስር መሆኑ ፕሮጀክቱ ለግንባታ የተመረጠበት ዋናው ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የእንጦጦ – 4 ኪሎ ኮሪደር ልማት የመንግስት ተቋማት፣ መስሪያ ቤቶች፣ ታሪካዊ ስፍራዎች እንዲሁም ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት ስፍራ መሆኑን አንስተዋል።

የኮሪደር ልማቱ መሰረተ ልማቶችን እና አገልገሎት ሰጭ ተቋማትን ለማስተሳሰር ያለውን ፋይዳ በመረዳት በአጭር ጊዜ ደረጃውን ጠብቆ እንዲገነባ ተደርጓል ነው ያሉት።

ሁሉንም መሰረተ ልማቶች በማሟላት የተገነባው የእንጦጦ – 4 ኪሎ ኮሪደር ልማት እውን እንዲሆን ህብረተሰቡ፣ መንግስት እና የግል ተቋማት ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.