የውጭ ሀገር ዜጎችን በኢትዮጵያ የንብረት ባለቤት የሚያደርገው አዋጅ ኢንቨስትመንትን ለማጠናከር…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ሀገር ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሚሆኑበት አግባብ በአዋጅ መደንገጉ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ያሳድጋል አሉ የምጣኔ ሃብት ምሁራን።
ምሁራኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷የአዋጁ መጽደቅ የውጭ ሀገር ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ በሙሉ ልብ የመስራትንና የኢንቨስትመንት ልማቶችን የማቀላጠፍ አቅም ይጨምራል።
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር መሸሻ ዘውዴ (ረ/ፕ/ር)÷ የአዋጁ መደንገግ በርካታ የኢንቨስትመንት አማራጮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡
የውጭ ሀገራት ዜጎች በሙሉ አቅም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ማልማት ሲጀምሩ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ልምድ ለማካፈልና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ጉልህ ሚና አለው ያሉት ደግሞ በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሃብት መምህሩ አቶ አያኖ ጀዋሮ ናቸው።
በውጭ ዜጎች የኢትዮጵያን አዎንታዊ ስም የመገንባቱ ሒደት በርካቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎታቸው እንዲጨምር እንደሚያደርግም አስገንዝበዋል፡፡
ውሳኔው የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ክምችት በማሳደግ አልሚ ባለሃብቶችን የሚያበረታታ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በጀማል ከድሮ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!