ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሁሉም ባለድርሻዎች በጋራ ሲሰሩ ነው – አቶ መሀመድ እድሪስ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻዎች በጋራ ሲሰሩ ነው አሉ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፡፡
የሰላም ሚኒስቴር በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ችግሮች ወደ ግጭት ሳይሻገሩ ለማስቀረት ያለመ የውይይት መድረክ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡
አቶ መሀመድ እድሪስ በመድረኩ እንዳሉት÷ የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግ ሰላምን ማፅናት ያስፈልጋል ብለዋል።
የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ማጽናት የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት እንደሆነ ገልጸዋል።
ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ ገልጸው÷ ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው የጸጥታ አካላትን ጨምሮ ባለድርሻዎች በጋራ ሲሰሩ ነው ብለዋል።
ዘላቂ ሰላም ሲረጋገጥ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል።
መድረኩ በሀገራዊ የሰላም ግንባታ የግጭት አፈታትና ሀገር ግንባታ ዙሪያ ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ልማትን ለማጎልበት የሚያስችል ግልጽነትና ዝግጁነት ያለው አመራር ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በሀይማኖት ወንድይራድ