Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

እውቅናው በ4 ኪሎ እንጦጦ፣ በጉለሌ የእፅዋት ማዕከል ኮሪደር ልማትና የእንጦጦ ወዳጅነት አደባባይ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ነው የተሰጠው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት÷ ራዕዩን ተጋርተው ደማቅ ታሪክ ለጻፉ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሠራተኞች ለዝናብና ቁር ሳይበገሩና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ መጪው ትውልድና መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚኮራበትን አስደናቂ ሥራ በመስራታቸው ታሪክ ሲዘክራችው ይኖራል ብለዋል።

በተለይም የወንዝ ዳርቻ ልማት ከ2012 ዓ.ም አንስቶ የውጭ መንግስታትንና ደጋፊ አካላትን እገዛ በመጠየቅ በርካታ ጥረት ቢደረግም በአምስት ዓመታት ከ2 ኪሎ ሜትር በላይ መስራት እንዳልተቻለ አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ እራሳችን ቆርጠን ስንገባበት 45 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻና 1 ሺህ ሔክታር መሬት የሚሸፍን ልማት በሰባት ወራት ጊዜ ውስጥ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ አሳክተናል ነው ያሉት፡፡

ሥራው በኢትዮጵያ ልጆች ዲዛይነርነት፣ አርክቴክትነት፣ መሪነትና አስተባባሪነት በታቀደው ልክ መከናወኑን አመልክተዋል፡፡

ለዚህም ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ መልኩ ለማበልፀግ ባላቸው ራዕይ የሃሳቡ አመንጪና ለሥራው ልዩ ትብብር ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የልማቱ ዋነኛ አጋር ለሆኑት ባለሃብቶች፣ አመራሮች፣ ሠራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ ማህበራትና ነዋሪዎችን ማመስገናቸውንም የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.