Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለብርሃን አይነ ሥውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለብርሃን አይነ ሥውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የብሬል ፕሪንተር፣ ዲጂታል ሪከርድስ እና ሌሎች ቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ትምህርት ትውልድን ለማነጽና ለነገ ሀገር ተረካቢ የሆነ የተማረ ዜጋን ለማፍራት ወሳኝ ተግባር በመሆኑን አመልክቷል፡፡

ለዚህም ጽ/ቤቱ በትምህርት ዘረፍ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ላለፉት 5 ዓመታት 35 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ ገንብቶ በርካታ ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ አድርጓል፡፡

የጥራት ደረጃቸውን ጠብቆ ከገነባቸው እጅግ ዘመናዊ ት/ቤቶች ውስጥ አንዱ አዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ብርሃን የአይነ ሥውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡

ትምህርት ቤቱ ከ400 በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከተለያዩ አካባቢዎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት የት/ቤቱን የመማር ማስተማር ሒደት፣ የት/ቤቱን እና የተማሪዎቹን ፍላጎት በቅርብ ክትትል በማድረግ በርካታ ተጨማሪ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በዛሬው ዕለትም የመማር ማስተማር ሒደቱን ሊያቀላጥፉ የሚችሉ የብሬል ፕሪንተር (ኢምቦሰር) እና ዲጂታል ሪከርድስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም በት/ቤቱ ውስጥ ለተማሪዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኘው ክሊኒክ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎች እና መመርመሪያ ሪኤጀንቶችን አበርከቷል፡፡

 

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.