Fana: At a Speed of Life!

ጃክ ግሪሊሽ ኤቨርተንን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኤቨርተን እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጃክ ግሪሊሽ ከማንቼስተር ሲቲ በውሰት ውል አስፈርሟል፡፡

ተጫዋቹ በመርሲሳይዱ ክለብ ለአንድ የውድድር ዘመን የሚያቆየውን የውሰት ውል ፈርሟል፡፡

የ29 ዓመቱ ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሊጉ 7 ጨዋታዎችን ብቻ ነበር በቋሚነት መጀመር የቻለው፡፡

ጃክ ግሪሊሽ በኤቨርተን ቆይታው 18 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስም ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡

ተጫዋቹ ከአስቶንቪላ ማንቼስተር ሲቲን ከተቀላቀለ በኋላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡

ግሪሊሽ ለውሃ ሰማያዊዎቹ ባደረጋቸው 157 ጨዋታዎች 17 ግቦችን ሲያስቆጥር፥ 23 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.