Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ38 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ ተመረተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ከ38 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ ተመርቷል አለ የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሃብት ቢሮ፡፡
በቢሮው የዓሣ ቴክኖሎጂ ባለሙያ አበበ ፈንታሁን እንዳሉት÷ በክልሉ ከተለያዩ ውሃማ አካላት የሚገኘውን የዓሣ ምርት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
የዓሣ ምርታማነትን ለማሳደግም በ2017 በጀት ዓመት 775 ሺህ 449 የተሻሻሉ የዓሣ ጫጩቶች መሰራጨታቸውን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ 376 ሺህ ሔክታር በሚሆን ውሃማ አካል ላይ የዓሣ ሃብት ልማት እየተከናወነ መሆኑን ባለሙያው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት 38 ሺህ 732 ቶን ዓሣ መመረቱን ጠቁመው ÷ የዓሣ ምርትን በቀዝቃዛ የትራንስፖርት ሰንሰለት ለገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.