በኦሮሚያ ክልል የማር ምርትን ለማሳደግ …
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የንብ ማነብ ሥራን በዘመናዊ መንገድ በማከናወን የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በክልሉ ግብርና ቢሮ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ቴክኒካል አስተባባሪ አቶ ጎሞሮ ደሬሳ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ከማር ምርት የሚገኘውን ገቢ ይበልጥ ለማጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የኦሮሚያ ክልልን የማር ምርት ማዕከል ለማድረግ እየተተገበረ የሚገኘው ኢኒሺዬቲቭ በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱን አንስተዋል፡፡
የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ የተከናወነው ባሕላዊ የንብ ማነብ ሥራን ወደ ዘመናዊ የመቀየሩ ሒደት አበረታች መሆኑን አመልክተዋል፡፡
አሁን ላይም የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን አጠናክሮ በማስቀጠል ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ለዚህም ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን ማሰራጨትና የገበያ ትስስር መፍጠር ላይ ትኩረት መደረጉን አብራርተዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 55 ሚሊየን በላይ ዘመናዊ የንብ ቀፎ እና 944 ሺህ በላይ የሽግግር የንብ ቀፎ ለማሰራጨት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የማር ምርት ላይ እሴትን በመጨመር አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆንና የገበያ ትስስር ላይ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ለመፍታት በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ጠቅሰዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 169 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት መገኘቱን ጠቁመው ÷ በ2018 በጀት ዓመት 180 ሺህ ቶን ማር ለማምረት በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!