Fana: At a Speed of Life!

ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓትን ለማጠናከር እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዲጂታል የፋይናንስ ሥርዓትን ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፡፡

3ኛው የዕውቀት ጉባዔ “የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጠራዎችን በመጠቀም ለፋይናንስ ዘርፉ አዳዲስ ገበያዎችን እና ማሳያዎችን መክፈት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ ማሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷የፋይናንስ ሥርዓቱን ወደ ዲጂታል በመቀየር ሁሉም ዜጋ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኝ በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውሎት መረጃን ለማደራጀት እና የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓትን አስተማማኝ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት፡፡

በዘርፉ ያለውን አቅምና ዲጂታል የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ ለዜጎች ቀልጣፋና ተአማኒ የፋይናንስ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ኃላፊ መፍትሄ ታደሰ በበኩላቸው÷የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓትን ማሳደግ ወጣቶችን ለማብቃትና ፈጠራን ለማበረታታት ያግዛል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እያሻሻለቻቸው የሚገኙ የተለያዩ ፖሊሲዎች ለዲጂታል ፋይናንስ ዕድገት ትልቅ በር የከፈቱ ናቸው ያሉት ደግሞ የክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙኒር ዱሪ ናቸው፡፡

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.