Fana: At a Speed of Life!

በመኸር ወቅት 50 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምርት ወደ መጠባበቂያ ክምችት ይገባል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተያዘው የ2017/18 ዓ.ም የመኸር ወቅት 50 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምርት ወደ መጠባበቂያ ክምችት ለማስገባት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፡፡

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከተቀመጡ ግቦች መካከል የመጠባበቂያ ክምችት አቅምን ማሳደግ ዋነኛው መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በግብርና ምርታማነት የምታስመዘግበው እመርታ የአደጋ ጊዜ የመጠባበቂያ ክምችትን አቅም በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።

የክልል መንግስታትም የመጠባበቂያ ክምችት አቅም በማሳደግ የዕለት ደራሽ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚያቀርቡበት አሰራር ተዘርግቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም የመጠባበቂያ እህል ክምችት የሰብል ምርታማነትን አቅም ማሳደግ የሚያስችል የ3 ቢሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለክልሎች መተላለፉን ኮሚሽነሩ አንስተዋል።

ለዚህ ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ አስተባባሪ ኮሚቴ መዋቀሩን ጠቅሰው፥ የፋይናንስ እጥረት የሚያጋጥማቸውን ክልሎች ለመደገፍ እንደሚያግዝም አብራርተዋል፡፡

ክልሎች የሰብል ምርታማነትን በማሳደግ ለመጠባበቂያ የሰብል ክምችት የሚውል ምርት ለኮሚሽኑ እንደሚያስተላልፉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.