በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት በሀገራዊ ምክክሩ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ የዳያሰፖራ አባላት በአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ኮሚሽኑ ዳያስፖራውን የምክክር ሒደቱ አካል ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው ጉዳይ አጀንዳቸውን በመስጠት በአካል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡
በዚህ መሰረትም በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከፈረንጆቹ ነሐሴ 30 ቀን 2025 ጀምሮ በዋሽንግተን ዲሲ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ ይካሄዳል፡፡
በተመሳሳይ በካናዳ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከፈረንጆቹ መስከረም 6 ቀን 2025 ጀምሮ በቶሮንቶ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡
ስለሆነም በሰሜን አሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ምዕራፍና የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች በሚመረጡበት መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሌላ በኩል በምክክር መድረኩ ላይ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዳያስፖራዎች ከታች በተቀመጡት ሊንኮች መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ተጠቅሷል፡፡
በዕለቱም ሀገራዊ መግባባት ሊደረስባቸው የሚገቡ አጀንዳዎች በመያዝ በሒደቱ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩ የዳያሰፖራ አባላት ፡-
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeqdKXQnsXwYXmtMigBiW7kxo7QgiYBiQRjWBrWehdVjHNNdA/viewform
በካናዳ ለሚኖሩ የዳያሰፖራ አባላት ፡-
https://forms.gle/y1kwixvgRVbdGiK99
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!