Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል ከ800 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ800 ሺህ በላይ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው አለ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ደስታ ለገሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ በ14 ዘርፎች እየተከናወነ የሚገኘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 800 ሺህ ወጣቶችን በማሳተፍ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ወጣቶች በችግኝ ተከላ፣ በቤት እድሳት፣ በደም ልገሳ እና በሌሎች ሰው ተኮር ሥራዎች በመሳተፍ ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ400 ሺህ በላይ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ÷ በዚህም ከ900 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በክረምቱ በሚከናወነው ዘርፈ ብዙ የበጎ ፈቃድ አገልገሎት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለማዳን ታቀዶ በትብብር እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መተሳሰብንና አብሮነትን የሚያጠናክር በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ባህል ሊያደርገው እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.