Fana: At a Speed of Life!

እየተፈተነ ያለ እናትነት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ኢየሩሳሌም ተስፋይ ሁለት ልጆቿ የሰረበራል ፓልሲ (ሲፒ) ተጠቂ ናቸው።
ይህ የልጆቿ የጤና ችግር አስቸጋሪ የእናትነት ጊዜን እንድታሳልፍ አስገድዷታል።
ኢየሩሳሌም ከ10 ዓመት በፊት በሰላም የወለደችው ወንድ ልጇ 1 ዓመት ከስድስት ወር ሲሞላው ጤናማ እድገት እያሳየ አለመሆኑን ትገነዘባለች፡፡
በሁኔታው ግራ የተጋባችው እናት ህፃኑን ወደ ሆስፒታል ትወስደዋለች።
በዚህም የኤምአርአይ ምርመራ ተደርጎለት የጡንቻዎችን ቅንጅት በመግታት ለእንቅስቃሴ ችግር የሚያጋልጠው የሰረበራል ፓልሲ (ሲፒ) ተጠቂ መሆኑ ታረጋግጣለች።
ህመሙን ሲጠራ እንኳን ሰምቸው አላውቅም የምትለው እናት ኢየሩሳሌም፤ ህክምናው አስቸጋሪ እንደሆነ በሚነግረለት ሰረበራል ፓልሲ ህመም ተጠቂ መሆኑ ሲነገራት በጣም እንዳዘነች ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች፡፡
ህፃኑ ልጅ ህክምናውን እየተከታተለ በነበረበት ወቅት ከሰረበራል ፓልሲ ጋር ተያይዞ የሚጥል ህመም አጋጥሞታል።
የኢየሩሳሌም ፈተና በዚህ አላበቃም የበኩር ልጇ ህመም በሁለተኛ ሴት ልጇ ላይም ተከሰተ።
እናት ከመጀመሪያው ልጇ ሁኔታ ግንዛቤ በመውሰድ የህፃኗን የጤና ሁኔታ በትኩረት ስትከታተል ህፃኗ የሁለት ወር እድሜ እያለች የሰረበራል ፓልሲ ምልክት ታይባታለች።
በዚህም ህፃኗ በሆስፒታል በተደረገላት ምርመራ እንደ መጀመሪያ ልጇ ሁሉ የሰረበራል ፓልሲ ተጠቂ መሆኗን አረጋገጠች።
የሁለቱ ልጆች የጤና ችግር ኢየሩሳሌምን ሀዘን ውስጥ ከመክተት ባለፈ ነገሮች የበለጠ ውስብስብና ከባድ እንዲሆንባት አደረገ።
የልጆቹ የጤና ሁኔታ እንዲህ ፈተና በሆነበት ወቅት ላይ ደግሞ አባታቸው ቤተሰቡን ጥሎ መጥፋቱ የኢየሩሳሌምን እናትነት ፈተና የበዛበት አድርጎታል።
እንደ ህፃናት መቦረቅ እና መጫዎት የማይችሉት የ5 እና የ10 ዓመት ልጆቿ ልዩ እንክብካቤ የሚፈልጉ መሆናቸው ተንቀሳቅሳ መስራትም ሆነ ጉዳይዋን መፈፀም አላስቻላትም።
በቤት ውስጥ ቀለል ያሉ የፊዚዮ ቴራፒ ህክምና እና ሌሎች ድጋፎችን ለልጆቿ እያደረገች የምትገኘው እናት ኢየሩሳሌም ተንቀሳቅሳ ባለመስራቷ ለችግር ተጋልጣለች፡፡
ልጆቿ የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ ጽኑ ፍላጎት ያላት ኢየሩሳሌም የፊዚዮ ቴራፒ ባለሙያዎች በሙያቸው እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ደግሞ በገንዘብ እንዲረዷት ትማፅናለች፡፡
ድጋፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000223445687 ኢየሩሳሌም ተስፋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.