Fana: At a Speed of Life!

አስቶን ቪላ እና ኒውካስል ዩናይትድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶን ቪላ እና ኒውካስል ዩናይትድ ያለምንም ግብ አቻ ተለያዩ፡፡

ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ አስቶን ቪላ በሜዳው ቪላፓርክ ኒውካስልን አስተናግዷል።

በጨዋታው ኤዝሪ ኮንሳ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

የተጫዋች ብልጫ የነበረው ኒውካስል ያገኘውን አጋጣሚ መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር 11 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ባለፈው የውድድር ዓመት ደካማ እንቅስቃሴ የነበረው ቶተንሃም ዘንድሮ ወደ ሊጉ ካደገው በርንሌይ ጋር ይገናኛል።

እንዲሁም ብራይተን ከፉልሃም፣ ሰንደርላንድ ከዌስትሃም በተመሳሳይ ሰዓት ይጫወታሉ።

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ወልቭስ ከፔፕ ጓርዲዎላው ማንቼስተር ሲቲ ጋር የሚያገናኘው ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

በትናንትናው ዕለት በተደረገው የሊጉ መጀመሪያ ጨዋታ ሊቨርፑል በርንማውዝን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.