ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለብሔራዊ ጥቅም…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ህግ የተቀመጡ መብቶቿንና ብሔራዊ ጥቅሟን በዘላቂነት እንድታስጠብቅ መሰረት የጣለ ነው አሉ ምሁራን።
ብዙ ፈተናዎችን ያለፈው የሕዳሴ ግድቡ ኢትዮጵያ ለዘመናት የተነፈገችውን በዓባይ ወንዝ የመጠቀም መብትን ያረጋገጠ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿ ብሔራዊ ጥቅሞቿን በዘላቂነት ማስጠበቅ የምትችልበትን መሠረት የጣለ መሆኑንም ተናግረዋል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ኢኮኖሚ መምህር ፍቃዱ ቶሎሳ (ዶ/ር) የግድቡ መጠናቀቅ ብዙ ለውጦችን ይዞ ይመጣል ብለዋል።
በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም አዲስ ስምምነቶች እንዲፈጠሩ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።
ግድቡ የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ዋጋ እንደሌላቸው አረጋግጧል ያሉት ፍቃዱ ቶሎሳ (ዶ/ር)÷ ከአሁን በኋላ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምን በተመለከተ የጋራ ትብብርን መሰረት ያደረጉ አዳዲስ ስምምነቶች ይፈጠራሉ ነው ያሉት።
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ህግ መምህር እውነቱ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ የግድቡ የምረቃ ዋዜማ ላይ መገኘት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ህግ የተቀመጡ በተፈጥሮ ሀብት የመጠቀም መብቶቿን ያረጋገጠችበት መሆኑን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ በወንዞቿና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ግድቡ በጎ ተጽዕኖ ማሳደሩን ገልጸው÷ ይህም ከአጎራባችና ሌሎች ሀገራት ጋር የተፈጥሮ ሀብትን በትብብር በመጠቀም የተሻለ ግንኙነት እንዲኖራት ያስችላል ብለዋል።
በተስፋየ ምሬሳ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!