11 የፖለቲካ ፓርዎች አንድ ጥምር ሀገር አቀፍ ፓርቲ መሰረቱ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምርጫ ቦርድ የተመዘገቡ 11 የተለያዩ የፖለቲካ ፓርዎች አንድ ጥምር ሀገር አቀፍ ፓርቲ መስርተዋል፡፡
ጥምር ፓርቲ የመሰረቱት አገው ለፍትሕና ዴሞክራሲ፣ አገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ አፋር ነፃ አውጭ ግንባር ፓርቲ፣ ከጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ እና የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ናቸው፡፡
ፓርቲዎቹ በዛሬው ዕለት የምስረታ ጉባዔን እያካሄዱ ነው።
ፓርቲዎቹ ለመጣመር የሚያስችላቸውን መስፈርት ለማሟላት እና አስቻይ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ባለፈው አንድ ዓመት ዝግጅቶች ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የፓርቲዎቹ ጥምረት ለሀገር ሰላም፣ ዕድገትና ክብር የሚሰራ ፓርቲ ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።
በመስራች ጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ÷ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ልዩነታቸውን በማጥበብ እርስ በርስ በመከባበር መርህ አንድ መሆናቸው የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
ጥምረታቸው የተስፋ፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲ መጎልበት ምሳሌ መሆኑን ጠቅሰው፤ ቦርዱ ተገቢውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በቅድስት አባተ