Fana: At a Speed of Life!

ለብሔራዊ መግባባት የምሁራን አስተዋጽኦ …

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤምሲ) ምሁራን ለብሔራዊ መግባባት የበኩላቸውን አስዋጽኦ ማድረግ ይገባቸዋል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡

ኮሚሽኑ “የምሁራን ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል ርእሰ ጉዳይ በአማራ ክልል ከሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉ ምሁራን የተሳተፉበት ውይይት በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ ምሁራን ሀገር የምትድንበትን ሃሳብ ማዋጣትና ለምክክሩ የበኩላቸውን ሚና መጫዎት ይኖርባቸዋል።

እንደ ሀገር ውይይት ባህል የሆነበት ማኅበራዊና ፖለቲካዊ አውድ ለመፍጠር ምሁራን በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ  አበርክቷቸውን ሰፊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እስካሁን ያካነወናቸው ተግባራትን በተመለከተ ገለፃ ተደርጓል፡፡

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.