Fana: At a Speed of Life!

የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት አገልግሎትን ውጤታማነት ያሳድጋል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደመወዝ ማሻሻያው ቀልጣፋ እና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት መስጠት ያስችላል አሉ የምጣኔ ሃብት ምሁራን፡፡

የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የደመወዝ ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡

መንግስት የኑሮ ውድነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የመንግስት ሠራተኞችን የኢኮኖሚ ሁኔታ በማጤን የሰጠው ምላሽ የሚበረታታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ማሻሻያው ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታልም ነው ያሉት፡፡

የምጣኔ ሃብት ምሁሩ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር) በበኩላቸው ÷ የደመወዝ ማሻሻያው ሠራተኞች ከብልሹ አሰራር በመራቅ ሥራቸውን ጠንቅቀው እንዲከውኑ ያስችላል ብለዋል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ማሻሻያ ትግበራ ሒደት ላይ ውጤትን መሠረት ያደረጉ ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉም ጠቁመዋል።

በዘላቂነት በሕብረተሰቡ ዘንድ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለማሻሻል መንግስት በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ምሁራኑ አስገንዝበዋል፡፡

በሲፈን መኮንን

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.