የትሪሊየን ዶላር ገበያዎች እና የንቁ ዜጋ ሚና
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ሀሽታጎችን በመጠቀም ለሀገራቸው አምበሳደር መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ዓለም አቀፍ የጥናት ተቋማት በፈረንጆቹ 2030 በዓለም አቀፍ ደረጃ የቱሪዝም፣ የፋሽን ኢንዱስትሪ፣ የስብሰባ መስተንግዶ እና የባህላዊ ምግቦች ጉብኝት የ1 ትሪሊየን ዶላር ገበያ እንደሚሆን ይጠቁማሉ።
የሀገራት ዋናው ጥያቄ የሚሆነው ታዲያ ያለኝን ሀብት ገልጬ፣ መንዝሬ የዚህ ገበያ ተቋዳሽ ለመሆን ምን ማድረግ አለብኝ የሚል ሲሆን ይህም የመንግስታት ትልቅ ተልዕኮ ነው፡፡
በዲጂታል ዓለም ውስጥ የንቁ ዜጋ ኃላፊነት እና አንደኛው የተሳትፎ አይነት የሚሆነው ደግሞ ሀገሬ የዚህ ተቋዳሽ እንድትሆን ያላትን ሀብት ለዓለም እንዴት ላሳይ፣ ላሳውቅ፣ እንዴትስ ግንዛቤ ልፍጠር የሚለው ይሆናል፡፡
ለዚህም ከታች የተዘረዘሩትን ሀሽታጎች በመጠቀም እና በማሳደግ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው አምባሰደር መሆን ይጠበቅባቸዋል።
1ኛ. #VisitEthiopia
የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ቅርሶች፣ ባህል እና መልክዓ ምድሮች ያስተዋውቃል፣ የሀገራችንን ዓለም አቀፋዊ ገጽታ እንደ ልዩ አፍሪካዊ መዳረሻ ያሳድጋል።
2ኛ. #BuyEthiopian እና #MadeInEthiopia
የኢትዮጵያን ምርቶች ከባህላዊ የፋሽን አልባሳት፣ ቡና እና ዕደ-ጥበብ እስከ አየር መንገድ እና ግብርና ውጤቶች ያስተዋውቃል፣ ኢኮኖሚውን ይደግፋል፣ የወጪ ምርትን ያሳድጋል እንዲሁም የምርት ስም (brand) ኩራትን ይገነባል።
3ኛ. #MeetInEthiopia
ኢትዮጵያን በአጠቃላይ እና አዲስ አበባን ጨምሮ በለውጥ ላይ ያሉ ከተሞቿን ለዓለም አቀፍ ዝግጅቶች እና ኹነቶች ማዕከል የመሆን እና የማስተናገድ አቅሟን እና በአፍሪካ ዲፕሎማሲ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ትብብር ያላትን ሚና ያስተዋውቃል።
4ኛ #EatInEthiopia
የኢትዮጵያን የተለያዩ ባህላዊ ምግቦች በማጉላት፣ የምግብ አሰራር ቱሪዝምን በማስተዋወቅ እና የሀገራችን የምግብ ጣዕሞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤን ይፈጥራል።
5ኛ #InvestInEthiopia
እንደ ግብርና፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ባሉ ዘርፎች የሀገሪቱን ሰፊ የኢንቨስትመንት እድሎችን ያስተዋውቃል።
#VisitEthiopia
#BuyEthiopian
#MadeInEthiopia
#MeetInEthiopia
#EatInEthiopia
#InvestInEthiopia