የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለማዕድን ዘርፍ ርዕይ መሳካት ዐቢይ ሚና እንዳለው እያስመሰከረ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለማዕድን ዘርፍ ርዕይ መሳካት ዐቢይ ሚና እንዳለው እያስመሰከረ ይገኛል አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ የሚገኘውን የኩርሙክ ዘመናዊ የወርቅ ፋብሪካና በአሶሳ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከአንድ አመት በፊት ወደ አሶሳ አቅንተው እንደነበር አስታውሰው፥ ዛሬ በከተማዋ ያየነው ባለፈው አመት ካየነው በፍፁም ተቃራኒ ነው ብለዋል።
የኮሪደር ልማት ስራው ውጤቱ የሚታይና የከተማዋ ገጽታ የተለወጠበት መንገድ ጥሩ ጅማሮ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአሶሳ በተወሰኑ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቀት የሚገኘውና በማሽን የታገዘው የኩርሙክ ዘመናዊ ወርቅ ፋብሪካ አስደናቂ የሥራ ውጤት ነው ብለዋል።
ፋብሪካው በሚቀጥለው አመት በግማሽ አቅሙ ማምረት እንደሚጀምር ገልጸው፥ የክልሉን ሰፊ የወርቅ አቅም የሚያሳይ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ከባለፈው አመት ጉብኝታችን በኋላ ያየነው እድገት የሚበረታታ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በጎ ተጽዕኖው በመላው ክልሉ የሚታይ እንደሆነ ነው የገለጹት።
መሰል ፕሮጀክቶች ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተደምረው የሀገራዊ ብልጽግናችን መገንቢያ ጡቦች ናቸው ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ማዕድን በብዝኃዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላልም ነው ያሉት፡፡
የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለዚህ ርዕይ መሳካት ዐቢይ ሚና ያለው መሆኑን እያስመሰከረ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጉብኝታቸው ጎን ለጎን አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!