Fana: At a Speed of Life!

ብልፅግና ፓርቲ ዘመን ተሻጋሪ ድሎችን እያስመዘገበ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልፅግና ፓርቲ እያከናወነ በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ሥራ ዘመን ተሻጋሪ ድሎችን እያስመዘገበ ነው አሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።

በክልሉ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የቆየው የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቅቋል።

አቶ ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ብልፅግና ፓርቲ የትላንት ጉድለቶችን መሙላት እንዲሁም የዛሬን ትውልድ መረታዊ ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በዚህም ለመጪው ትውልድ መሰረት የሚጥሉ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እውን እያደረገ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በሐረሪ ክልል የተሰሩ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች ማሳያ መሆናቸው ጠቅሰው ÷ ለስኬቶች ቀጣይነት አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይም ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር ብሔራዊ ጥቅም እንዲጠበቅ መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በቁርጠኝነት በመከላከልና የአገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ ሁለተናዊ ብልፅግና እንዲረጋገጥ መስራት ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል።

አመራሩ ለሕዝብ የተገቡ ቃሎችን በተግባር በመፈጸም ውጤታማነትን ለማረጋገጥና በተሰማራበት መስክ ሁሉ ዓርበኛ እንዲሆን አጽንኦት መስጠታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.