ከ290 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ 3ቱ ብቻ ፈቃዳቸው ጸንቷል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዳግም ምዝገባ ከተመዘገቡ 290 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ሶስቱ ብቻ መስፈርቱን አሟልተዋል አለ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን።
በባለስልጣኑ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሕይወት አሰፋ እንዳሉት÷ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመመዝገብ በተዘጋጀው አዲሱ የዳግም ምዝገባ መገምገሚያ መስፈርት 375 ተቋማትን ለመመዝገብ ታቅዶ 290 ተቋማት ተመዝግበዋል፡፡
290 ተቋማት ተመዝግበው በተካሄደው የመጀመሪያ ዙር ግምገማ መስፈርቱን ያሟላ ተቋም ባለመኖሩ መስፈርቱ ተሻሽሎ ሁለተኛ ዙር ግምገማ መካሄዱን አንስተዋል፡፡
መንግስት ተቋማቱ ራሳቸውን አብቅተው በትምህርት ሥርዓቱ እንዲቀጥሉ በማሰብ 3ኛ ዙር መስፈርቱን በማሻሻል ዝቅተኛውን መስፈርት እንዲያሟሉ ዕድል መሰጠቱንም አስታውሰዋል፡፡
በዚህም 3 ተቋማት ፤ በ3 ካምፓስ በ17 የትምህርት መስክ ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው ፈቃዳቸው መጽናቱን ተናግረዋል።
በ12 ወራት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን እንዲያሟሉ ቅድመ ሁኔታ የተሰጣቸው ደግሞ 25 ተቋማት ፤ በ37 ካምፓስ በ146 የትምህርት መስክ የተገጓደሉትን እንዲያሟሉ መደረጉን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል በ6 ወራት እንዲያሟሉ ውሳኔ የተላለፈባቸው ተቋማት መኖራቸውን ጠቁመው ÷ 85 ተቋማት ቀርበው መመዝገብ ባለመቻላቸው በራሳቸው ጊዜ ከሥርዓቱ መውጣታቸውን አመልክተዋል፡፡
በተካልኝ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!