Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ከኮንሶ ወደ ሞጆ በሬ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኤፍኤስአር የጭነት ተሽከርካሪ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ም/ል ኮማንደር ኤሊያስ ሜንታ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

አደጋው የደረሰው በወረዳው ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ሌሊት 7፡30 ገደማ ሲሆን፥ የአሽከርካሪውና የረዳቱ ህይወት ወዲያው አልፏል፡፡

በተሽከርካሪው ላይ ተጭነው የነበሩ 17 በሬዎች በሙሉ መሞታቸውን ገልጸው፥ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ነው ም/ል ኮማንደር ኤሊያስ የገለጹት።

በማስተዋል አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.