አህጉራዊ ትስስርን እውን ለማድረግ የሚዲያዎች አበርክቶ ከፍተኛ ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አህጉራዊ ትስስርን እውን ለማድረግ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ትልቅ አበርክቶ አለው አሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ።
15ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኮሙኒኬሸን ማህበር ጉባዔ “ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለአፍሪካ ትስስር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር ) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ኢትዮጵያ አህጉራዊ ውህደትን ለማረጋገጥ በመሰረተ ልማት፣ በንግድ፣ በሕዝብ ለሕዝብ ትስስርና ሌሎች ጉዳዮች በትኩረት እየሰራች ነው፡፡
በመገናኛ ብዙሃኖቿም በምስራቅ አፍሪካ በብዛት በሚነገሩት ኪስዋሂሊና ዓረብኛ ቋንቋዎች እየሰራች ትገኛለች ነው ያሉት፡፡
የምንመኘውን አህጉራዊ ትስስር እውን ለማድረግ የጋራ ማንነታችንና የተጋመደ እጣፈንታችንን የሚያመላክቱ ታሪኮችን መተረክ ይገባል ብለዋል፡፡
አህጉራዊ ትስስሩ ያለሚዲያና ኮሙኒኬሽን የነቃ ተሳትፎ እውን ሊሆን እንደማይችልም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሚዲያዎች የጋራ ማንነትን ለመግለጽና ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያስችሉ ጠቁመው ÷ ኮንፈረንሱ በጋራ የትስስር አጀንዳዎች ላይ ለመምከር ዕድል ይሰጣል ነው ያሉት ።
የማህበሩ ፕሬዚዳንት ማርጋሬት ጁኮ (ፕ/ር) በበኩላቸው ÷ ጉባዔው የቴኮኖሎጂ መራቀቅ በሚዲያው ዘርፍ ይዞ የሚመጣውን አሉታዊ ተጽዕኖ የሚገቱ እውቀቶች የሚዋጡበት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመራኦል ከድር
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!