Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ስልክ እንዳይዙ ከለከለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ደቡብ ኮሪያ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ ስማርት ስልኮችን እንዳይዙ የሚከለክል ህግ አፅድቃለች፡፡

ህጉ በፈረንጆቹ 2026 ተግባራዊ መሆን ይጀምራል ተብሏል፡፡

የክልከላ ህጉ ህፃናት እና ታዳጊዎች ለዘመናዊ ስልክ ሱስ መጋለጣቸው በጥናት መረጋገጡን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ርምጃው ተማሪዎችን ከስማርት ስልክ ሱሰኝነት ለመጠበቅ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የሀገሪቱ የህግ አውጪዎች፣ ወላጆች እና አስተማሪዎች ዘመናዊ ስልኮች የህፃናትን የጥናት ጊዜ በመሻማት ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።

ይሁን እንጂ ዘመናዊ ስልኮችን የመጠቀም ሱስን ለመከላከል ከጸደቀው ህግ በተጨማሪ የስነ ልቦና ምክሮችን መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በመንግስት ጥናት መሰረት ከሀገሪቱ ህዝብ 25 በመቶ የሚሆነው የስማርት ስልኮች ሱስ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እድሜያቸው ከ10 እስከ 19 ከሚሆኑት ታዳጊዎች ደግሞ 43 በመቶ ያህሉ የዘመናዊ ስልክ ሱስ እንዳለባቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

 

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.