መዲናዋ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ የወርቅ ተሸላሚ ሆነች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ ከተማ በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው ፍጥነትን ማስተዳደር ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች።
በብሉምበርግ ፊላንትሮፒ በፍጥነት አስተዳደር ላይ ህጎችን በማውጣት እና ተግባራዊ በማድረግ የመንገድ ደህንነትን ያሻሻሉ ከተሞችን አወዳድሮ እውቅና ሰጥቷል።
በዚህም መዲናዋ ብሉምበርግ ኢኒሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲ ባዘጋጀው ውድድር የወርቅ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
ከ2015 እስከ 2017 በኢንሼቲቩ ውስጥ ያሉ ከተሞች እና አስተዳደሮች በዓለም ጤና ድርጅት የሚመከሩ የፍጥነት ገደቦችን ወስደው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ከተማችን ባስመዘገበችው ተጨባጭ ውጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ የወርቅ ሽልማት አሸናፊ በመሆኗ ታላቅ ክብር ተሰምቶናል ብለዋል።
እውቅናው ከተማችን ፍጥነትን ለማስተዳደር እና የመንገድ ደህንነት ለማሻሻል የምትወስደውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ዳግም የሚያረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተማዋ የፍጥነት አስተዳደርን በፈጠራ እና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የታገዘ በማድረግ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል።
በተለይም ከተማ አቀፍ አውቶማቲክ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎች እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንሰፖርት ስርዓት ተግበራዊ ይደረጋል ነው ያሉት።
በሽልማቱ የተገኘው 100 ሺህ ዶላር በቀጣይ የከተማዋ መንገዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ጤናማ እና ለነዋሪው ተስማሚ ምቹ አካታች እንዲሆኑ ለሚያስችሉ ስራዎችን እገዛ ያደርግልናል ብለዋል።
የብሉምበርግ ኤልፒ እና የብሉምበርግ ግበረ-ሰናይ ድርጅት መስራች፤ የዓለም ጤና ድርጅት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና ጉዳቶች አምባሳደር እንዲሁም የኒው ዮርክ ከተማ 108ኛው ከንቲባ ማይክል አር ብሉምበርግ፤ በፍጥነት ማሽከርከር በሀገራቸው በየዕለቱ የ1 ሺህ 600 ሰዎች ህይወት ይቀጥፋል ነው ያሉት።
በፍጥነት አስተዳደር ውድድር ያሸነፉ ከተሞች ያከናወኗቸውን ውጤታማ ስራዎች በመለየት እና ልዩ ትኩረት እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ሰርተዋል ማለታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ አመልክቷል።
በአዲስ አበባ ከፍተኛ የተሽከርካሪ አደጋ የሚደርሳባቸው ቦታዎች እና ኮሪደሮች ተለይተው በመንገድ ዲዛይን እና ምህንድስና፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም የትራፊክ ቁጥጥር የመንገድ ደህንነት ማሻሻያ ስራዎች መተግበራቸው ተመላክቷል።
በውድድሩ አዲስ አበባ እና ቦጎታ የወርቅ አሸናፊ ከተሞች ሲሆኑ ቤንጋሉሩ፣ ቦነስ አይረስ፣ እና ጓዳላጃራ የብር እንዲሁም በሶስተኛ ደረጃ ካምፓላ፣ ሞምባሳ፣ እና ኪቶ የነሐስ ሽልማት አሸንፈዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!