Fana: At a Speed of Life!

ፋብሪካው ለግብርና፣ የማዕድን እና ለኢንዱስትሪ ዘርፎች ልማት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል – አቶ አህመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና የማዕድን ዘርፎች ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡

አቶ አህመድ ሺዴ ስምምነቱን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፤ የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ የሚያመርተው ዩሪያ ማዳበሪያ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ይውላል።

የማምረቻው አቅም እያደርገ ሲሄድ ደግሞ ወደ ውጪ መላክ እንደሚጀመር ገልጸዋል።

የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ተገንብቶ በካሉብ እና ኢላላ ያለውን የተፈጥሮ ጋዝ በግብዓትነት እንደሚጠቀም አብራርተዋል።

ማዳበሪያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዛ ወደ ሀገር እንደሚገባ አስታውሰው፤ የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ ይህንን የሚያስቀር ትልቅ ስትራቴጂክ ፋብሪካ ነው ብለዋል።

የተፈጥሮ ጋዝን በማልማት የማዕድን ዘርፍ ልማታችንን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ እና ለማዕድን ዘርፍ ልማታችን ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ነው ያሉት።

ይህም የሀገሪቷን ኢኮኖሚ እድገት በማፋጠን፣ የስራ ዕድል በመፍጠር፣ የግብርና ዘርፍ ልማቱን በማፋጠን፣ የማምረት አቅማችንን በመጨመር፣ የውጭ ምንዛሬ በማዳን እና ለአጠቃላይ ኢንዱስትሪ ልማት እገዛ የሚያደርግ ታሪካዊ ስምምነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱን ተከትሎ መሰረተ ልማቶች እንደሚገነቡ አንስተው፤ የተፈጥሮ ጋዝ ያለባቸው አካባቢዎች ማሕበረሰብ እንዲሁም መላው ኢትዮጵያን የልማት ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

ለኢትዮጵያ እድገት ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክት እና የቀጣናው የማዳበሪያ አቅርቦት ማዕከል ሆና እንድትወጣ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትላልቅ ኢንቨስትመንቶች እንዲመጡ እየሰሩ እንደሆነ አስታውሰው፤ ከግዙፉ ዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱ ለረዥም ዓመታት ሲሰራበት የነበረው ስራ ውጤት ነው ብለዋል።

መንግስት እድገትን ለማፋጠን የሚከተላቸው ፖሊሲዎች ውጤታማ እና ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ደረጃ ሊያስቀጥል የሚችል አቅም የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.