ጆዜ ሞሪኒሆ ከፌነርባቼ ጋር ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ ከፌነርባቼ ጋር መለያየታቸውን ክለቡ አስታወቀ፡፡
የቱርኩ ክለብ ዛሬ እንዳስታወቀው÷ ውሳኔው የተላለፈው ፌነርባቼ ትናንት ምሽት በቤኔፊካ ተሸንፎ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ውጭ መሆኑን ተከትሎ ነው፡፡
ጆዜ ሞሪኒሆ ከአንድ ዓመት በላይ ፌነርባቼን በዋና አሰልጣኝነት የመሩ ቢሆንም የቱርኩን ሱፐር ሊግ ሀያል ክለብ ውጤታማ ማድረግ አልቻሉም፡፡
ክለቡ ረቡዕ ምሽት በቤኔፊካ 1 ለ 0 ሽንፈት ካስተናገደ በኋላ ጆዜ ሞሪኒሆ ከክለቡ ጋር እንዲለያዩ መወሰኑን ጎል ዶት ኮም ዘግቧል፡፡
በሚኪያስ አየለ