“እንቁ ለጣትሽ ኦቪድ ለቤትሽ” ታላቅ የቤት ሽያጭ ገበያ ተከፈተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኦቪድ ሪል ስቴት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በልዩ ቅናሽ የመኖሪያ ቤትና የንግድ ሱቆች ሽያጭ ገበያ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡
የኦቪድ ግሩፕ ማርኬቲንግ ማኔጀር መቅደስ ቀደመ እንዳሉት ÷ ብዙዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ያለመው ኤክስፖ ለ7 ተከታታይ ቀናት በገርጂ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሳይት ቅጥር ግቢ ይካሄዳል፡፡
ኦቪድ ሪል ስቴት ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር በርካቶችን የቤት ባለቤት ያደረገ ልዩ ቅናሽ የቤት ገበያ አዘጋጅቶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
መርሐ ግብሩ በቤት ፈላጊዎች ጥያቄ መሰረት በዛሬው ዕለት ዳግም መከፈቱን ነው ያስገነዘቡት፡፡
ቤት ፈላጊዎች ከተዘጋጀው የአዲስ ዓመት ልዩ ቅናሽና ምቹ የአከፋፈል ዘዴ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!