Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ውስጥ ምርትን መግዛት የሥራ ዕድል በመፍጠር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ያሳልጣል – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር ውስጥ ምርትን መግዛት ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን የሚያሳልጥ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

 

ፕሬዚዳንት ታዬ በጥራት መንደር የተዘጋጀውን “የኢትዮጵያን ይግዙ” ሀገራዊ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ መርቀው ከፍተዋል።

 

ፕሬዚዳንቱ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሀገር ውስጥ ምርት መግዛትና መጠቀም የሀገራዊ ኢኮኖሚን የሚያደረጅ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ምርት ይግዙ ስንል የሀገር ውስጥ ምርቶችን ጥራት ለኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ድርሻ አሳድጉ ማለት ነው ብለዋል።
የሀገር ውስጥ ምርት ጥራትና ፍጥነት የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ለጤናማ ኢኮኖሚ መሰረት በመጣል መልካም የዕድገት ተስፋ ይሰጣል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ኤክስፖ የሀገር ውስጥ አምራችና ሸማቾችን በማገናኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዕድገት ምዕራፍ ላይ መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ÷ ኢትዮጵያ በሀገራዊ ሪፎርሙ ታግዛ አበረታች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ማስመዝገቧን ተናግረዋል።
የሀገር ውስጥ ምርትን መጠቀም ሀገራዊ ሀብትን በማባዛትና በማደራጀት የጎላ ትሩፋት ይኖረዋል ነው ያሉት።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.