የያቤሎ አየር ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የዘመናት የልማት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው -አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የያቤሎ አየር ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የዘመናት የልማት ጥያቄ ምላሽ የሰጠ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የያቤሎ አውሮፕላን ማረፊያን አገልግሎት በዛሬው ዕለት አስጀመሯል።
በዚሁ ወቅት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዳሉት መንግስት የመሰራተ ልማት ዝርጋታን በማፋጠን የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው።
ከመሃል ሀገር ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን በመሠረተ ልማት ተጠቃሚ በማድረግ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዘርፎች እኩል ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በቦረና አካባቢ የያቤሎ አየር ማረፊያ ተገንብቶ አገልግሎት መጀመሩ ቦረና ከአዲስ አበባ የነበረውን ረጅም መንገድ ያሳጠረ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
መንግሥት የህዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በተግባር ምላሽ እየሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል።