Fana: At a Speed of Life!

በተደጋጋሚ ድርቅ ሲፈተን የነበረው የቦረና ዞን በአዲስ ምዕራፍ ላይ ይገኛል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተደጋጋሚ ድርቅ ሲፈተን የነበረው የቦረና ዞን በአዲስ ምዕራፍ ላይ ይገኛል አሉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን፥ በዞኑ በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ድርቅ ዘላቂ መፍትሔን ለማበጀት በተጀመረው ፊና ፕሮጀክት አማካኝነት 14 ግድቦች መገንባታቸውን ተናግረዋል፡፡
በግድቦቹ አማካኝኝነት የአርብቶ አደሩ የውሃ እና የመኖ እጥረት እንዲቀረፍ ማስቻሉን ተመልክተናል ነው ያሉት፡፡
ፕሮጀክቱ ውሃን፣ መሬትንና ግጦሽን ማስተዳደር እንዲሁም ከህይወት ጋር አያይዞ ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጡ ማስቻል መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህንን የቦረና ህዝብ በተግባር ማሳየት ችሏል ብለዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የቦረና ህዝብ ለሌሎችም ጭምር ምሳሌ የሚሆን ስራ ሰርቷል ነው ያሉት፡፡
አሁን ላይ የቦረና አርብቶ አደሮች የድርቅ ስጋት እንደሌለባቸውና ከብቶች በጥጋብ ከመስክ ውለው እንደሚገቡ ገልጸው፥ በዞኑ ሁሉም ሙሉ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡
ይህንን ተግባራዊ ላደረጉ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ለቦረና ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.