Fana: At a Speed of Life!

የትውልድ ዐሻራ የተሰኘ የህዳሴ ግድብ የብስራት መልዕክት ማስተላለፊያ ቁጥር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትውልድ ዐሻራ የተሰኘ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የብስራት መልዕክት ማስተላለፊያና የገቢ ማስገኛ ቁጥር ይፋ ሆነ።
የግድቡ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) የብስራት ማስተላለፊያ ቁጥሩ በዛሬው እለት ይፋ በሆነበት ወቅት፤ ግድቡ የአንድነታችንና የፅናታችን ማሳያ የዘመናችን ዓድዋ ነው ብለዋል።
የግድቡ ፕሮጀክት ለአፍሪካም ምሳሌ መሆናችንን ዳግም ያሳየንበት ነው ሲሉ ገልጸው፤ ግድቡ እዚህ እስከሚደርስ የተሰራው የዲፕሎማሲ ስራ ውጤት አምጥቷል፤ አሸናፊም ሆነናል ነው ያሉት።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፅናትን፣ ጀግንነትን ያሳየንበት ፕሮጀክት ያሉት አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፤ በውስጥም በውጭም ያጋጠሙ ፈተናዎችን በማለፍ የጥረታችንን ፍሬ አይተናል ብለዋል።
ባለፉት አመታት 8100ን በመጠቀም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለግድቡ ዐሻራውን ሲያኖር መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን ደግሞ ግድቡ በመጠናቀቁ ሁሉም ሰው የተሰማውን ስሜት 8120 ላይ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚልክበት የብስራት ማስተላለፊያ ቁጥር እውን መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ አጭር የፅሁፍ መላኪያ አማራጭ ከዛሬ ነሐሴ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተጠቁሟል።
በሐመልማል ዋለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.