መጪዎቹ የጳጉሜን ቀናት…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተገባደደው ዓመት የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራትና የቀጣይ ሀገራዊ እቅዶች የሚተዋወቁባቸው መጪዎቹ የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ጳጉሜን-1 የጽናት ቀን
የጽናት ቀን “ጽኑ መሰረት ብርቱ ሃገር” በሚል መሪ ሀሳብ ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚተጉና ዋጋ የከፈሉ ኢትዮጵያውያንን በመዘከርና በማመስገን ይከበራል፡፡
ጳጉሜን-2 የህብር ቀን
የህብር ቀን “ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል ሀሳብ የኢትዮጵያን የብዝሃነትና የአንድነት ውበት እንዲሁም የአብሮነት እሴት በሚያጎሉ ዝግጅቶች ተከብሮ ይውላል፡፡
በዕለቱ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የቁሳቁስ፣ የማዕድ ማጋራት፣ የመማሪያ ቁሳቁስና መሰል ድጋፎችን በማድረግ አብሮነትን የሚያሳዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት ይከናወናሉ፡፡
ጳጉሜን-3 የእመርታ ቀን
የእመርታ ቀን “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ ባለፉት አመታት የተመዘገቡ ስኬቶችንና ለቀጣዩ አመት የተሻለ ስራዎች እንዲሰሩ በማሰብ ይከበራል፡፡
በግብርናው ዘርፍ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድንና ሌሎች ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ይወሱበታል፡፡
ጳጉሜን-4 የማንሰራራት ቀን
የማንሰራራት ቀን “ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ኢትዮጵያ በለውጥ የማንሰራራት ጅማሮ ላይ መሆኗን በሚያሳዩ ሁነቶች ይከበራል፡፡
ጳጉሜን-5 የነገው ቀን
የነገው ቀን “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ ሀሳብ የነገዋን ኢትዮጵያ በዲጂታል ለመገንባት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማውሳት የሚከበር ይሆናል፡፡
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!