የመውሊድ በዓል ሲከበር በተለመደው የመረዳዳት ባህል ሊሆን ይገባል – ጉባኤው
አዲስአበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል ሲከበር በተለመደው ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህል ሊሆን አለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ።
ጉባኤው ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ መታሳቢያ በዓል አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
የዘንድሮ መውሊድ በሁለት ታላላቅ ክስተቶች መሐል የሚከበር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ያለው ተቋሙ፤ የመጀመሪያ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና በየደረጃው የሚገኙ የምክር ቤቱ ድርጅታዊ መዋቅር ምርጫ ተከናውኖ ወደመቋጫው በደረሰበት ወቅት መከበሩ ነው ብሏል፡፡
ሌላው ደግሞ የአንድነታችን ምሰሶና የሕብረታችን ማሳያ፣ የጥረት፣ የጽናት እና የትብብር ምሳሌና ምልክት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ የምረቃ ጊዜውን በጉጉት በምንጠባበቅበት ሰሞን መከበሩ ነው ሲል ገልጿል።
የ1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል ሲከበር በተለመደው ኢትዮጵያዊ የመረዳዳት ባህል ሊሆን ይገባል ሲል ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ ጠቁሟል።
በተለይም በሕመም አልጋ ላይ እና በሕግ ጥላ ስር የሚገኙትን ወገኖቻችንን በመጠየቅ እና በማበረታታት፣ በተለያየ ችግር ውስጥ የሚገኙት ወገኖቻችን በዓሉን በደስታ ማክበር ይችሉ ዘንድ ያለንን በማካፈል መሆን አለበት ሲል አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
በዓሉ ሲከበር ለሀገራችን ሰላም፣ ለሕዝባችን አንድነት እና በረከት ከልብ የሆነ ዱዓ በማድረግ መሆን አለበት ነው ያለው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!