ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ፕሬዚዳንት ታዬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የትሩፋት እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።