የመውሊድ በዓል በሐረር እና ጅማ ከተሞች በድምቀት እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1ሺህ 500ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በሐረር ከተማ ከትላንት ምሽት ጀምሮ የነብዩ መሐመድን በጎነት፣ እዝነትና የፈፀሟቸውን መልካምነት በሚዘክሩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ ነው።
ህዝበ ሙስሊሙ የነብዩ መሐመድን አርአያነት በህይወት ዘመኑ ሁሉ መተግበር እንዳለበት ነው የበዓሉ ታዳሚዎች የገለጹት፡፡
በተመሳሳይ በዓሉ በጅማ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
የጅማ ከተማ ሙኒር መስጂድ ኢማም ሼኽ መሀመድ አባ ዲጋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ የመውሊድ በዓልን ስናከብር የነብዩን ፈለግ በመከተል ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በተሾመ ኃይሉ እና አብዱረህማን መሀመድ