የክልሉን ሕዝብ ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው – አቶ አወሉ አብዲ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ፡፡
በሰንዳፋ በኬ ከተማ በመንግስትና ሕዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡
አቶ አወሉ አብዲ በምረቀ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ የክልሉን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
በዛሬው ዕለት የተመረቁት ፕሮጀክቶች ከተማዋ የጀመረችውን የለውጥ ሒደት የሚያጠናክሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ለአገልግሎት ክፍት ከሆኑት ፕሮክቶች መካከል ት/ቤቶች እንዲሁም የገበያ፣ የእንስሳት ማድለቢያ እና የዶሮ እርባታ ማዕከላት ይገኙበታል፡፡
አቶ አወሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ገጽታን የሚገነቡ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በብዛትና በጥራት እየተገነቡ ለአገልግሎት እየበቁ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!