Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሮኒክ ግብይት ሥርዓትን ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግብይት በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት የሚያስገኘውን ጠቀሜታ ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ ነው አሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)።
ሚኒስቴሩ ”ኢ ኮሜርስ ለተሻለ ተወዳዳሪነት” በሚል መሪ ሃሳብ የኤሌክትሮኒክ ንግድ አገልግሎትን ለማዘመን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል።
ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ መንግስት የንግድ ሥርዓቱን ቀልጣፋና ተወዳዳሪ ለማድረግ በሰጠው ትኩረት የወጪ ንግድ ከፍተኛ ዕድገት እየተመዘገበበት ይገኛል።
በዓለም አቀፍ ገበያ ይበልጥ ተወዳዳሪ ለመሆን የንግድ እንቅስቃሴን በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራን ለማፋጠን ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡
በቀጣይም የኤሌክትሮኒክ ግብይትን የሚያሳልጡ የቁጥጥርና የአሰራር ማዕቀፎች ተዘጋጅተው እንደሚተገበሩ ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያ ሥላሴ በበኩላቸው ፥ የዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት በኤሌክትሮኒክ ግብይት መተማመንን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።
የኤሌክትሮኒክ ግብይት ዲጂታል ኢትዮጵያን በመገንባት ሒደት ትልቅ ሚና አለው ያሉት ደግሞ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አብዮት ባዩ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
በኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል መኒ ዋና ኦፊሰር አቶ ብሩክ አድሃና÷ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ለማስፋት ሰፊ የቴሌኮም መሰረተ ልማት መዘርጋቱንና የ4 ጂ እና 5 ጂ ኔትወርክ ማሻሻያ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.