የጽናት ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር ጳጉሜን 1 ቀን የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢቶች እየተከበረ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጭምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የጸጥታ አካላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመርሃ ግብሩ ላይ ታድመዋል።