የጽናት ቀን በጋምቤላ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ጳጉሜ 1 የጽናት ቀን ‘ጽኑ መሠረት፤ ብርቱ ሀገር’ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች የቀረቡ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡