Fana: At a Speed of Life!

የኅብር ቀን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኅብር ቀን እና የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተለያዩ ሁነቶች ተከናውነዋል፡፡
“ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው መርሐ ግብር በሪያድና አካባቢው የሚኖሩ ኢዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ታድመዋል፡፡
በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ “የምናከብረው ታሪካዊ በዓል በመንግስታችን እና ሕዝባችን ፅናት የሕዳሴ ግደብ ግንባታ መጠናቀቅን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
ብዝሃነት ጌጥ በመሆኑ ይህንን ጸጋ በመጠቀም ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በሳዑዲ የመኖሪያ ፈቃድ የተበላሸባቸውና ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ያለቅጣት መመለስ እንዲችሉ ኤምባሲው ለሀገሪቱ መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ኤምባሲው ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ለተወሰኑ ጊዜያት ዜጎች ከሀገሪቱ መውጣት እንዲችሉ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት መፍቀዱን አብስረዋል፡፡
በሪያድ የኢትዮጵያውያን ኮሚዩኒቲ ማህበር ዋና ሰብሳቢ ኡስታዝ ሱለይማን መሃመድ በበኩላቸው ÷ በሪያድና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
በቀጣይ በሚደረጉ ሀገራዊ የልማት ሥራዎች ዳያስፖራው እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በፕሮግራሙ ለሕዳሴ ግድብ መሳካት ሀገራዊ ግዴታቸውን ለተወጡ በሪያድና አካባቢው ለሚኖሩ የዳያስፖራ አባላትና ተቋማት እውቅና መሰጠቱን ኤምባሲው ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.