Fana: At a Speed of Life!

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው – የኢፌዴሪ አየር ኃይል 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው አሉ የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፡፡

ሌ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ግድቡ ተጠናቅቆ ለምረቃ በመብቃቱ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ግድቡንና የኢትዮጵያን አየር ክልል የማያስደፍር የአየር ሀይል ተገንብቷል ያሉት ዋና አዛዡ፥ ግድቡ የኢትዮጵያ ከፍታ ማብሰሪያና የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ ያረፈበት ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቦታው ተገኝቼ ግድቡ ለምርቃት በቅቶ በማየቴ ምትክ ሊገኝለት የማይችል ኩራት ተሰምቶኛልም ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የግድቡ መሠረተ ድንጋይ ከተቀመጠበት ጊዜ አንስቶ ለምርቃት እስከበቃበት ግዜ ድረስ የቀጠናውን የአየር ክልል በአስተማማኝ ሁኔታ በመጠበቅ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ካለፉት አመታት በተለየ ሁኔታ ተቋሙ የምድር አየር መከላከል አቅም ማሳደጉን ጠቅሰው፥በሰማይ የጠላትን ኢላማ ገና ከመነሻቸው ማውደም የሚችሉ ተዋጊ የጦር ጄቶችን መታጠቁን አመላክተዋል፡፡

ባጠረ ግዜ በላቀ ብቃት የመፈፀም እምቅ አቅምና ቴክኖሎጂውን መጠቀም የሚችል የሠው ኃይል አደራጅተን በማንኛውም ሰዓት የአየር ክልሉን የማያስደፍር የሀገር ኩራት የሆነ አየር ኃይል ተገንብቷል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.