Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በራሷ አቅም መጨረስ መቻሏ የሚደነቅ ነው – የፓኪስታን ሴኔት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፓኪስታን ሴኔት ኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በራሷ አቅም መጨረስ መቻሏ የሚደነቅ ነው አለ።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ታሪካዊ ምረቃና የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን አክብሯል።
በመርሐ ግበሩ በክብር እንግዳነት የተገኙት የፓኪስታን ሴኔት ሊቀ መንበር ዩሱፍ ረዛ ጊላኒ ÷ ኢትዮጵያ በተለያዩ የልማት መስኮች እያስመዘገበች ያለው ሁሉን አቀፍ ስኬት የሚደነቅ ነው ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር ) በበኩላቸው÷ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የኅብረትና የፅናት ውጤት መሆኑን አውስተዋል።
የሕዳሴ ግድብ የሕብረ ብሔራዊ አንድነትና የማሸነፍ ተምሳሌት ነው ያሉት አምባሳደሩ ÷ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስትም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.