የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሕዳሴ ግድብ በመመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
አገልግሎት በመልዕክቱ የዳግማዊ ዓድዋና የኢትዮጵያ ከፍታ ብስራት የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በመመረቁ መላው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች መደሰታቸውን ጠቅሷል፡፡
ለመላው ኢትዮጵያዊያንም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡