Fana: At a Speed of Life!

ኪን ኢትዮጵያ በራሺያ ሴንትፒተርስበርግ ከተማ የመጀመሪያውን መድረክ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኪን ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት የባህል እና የጥበብ መድረክ በሩሲያ ሴንትፒተርስበርግ ከተማ የመጀመሪያውን መድረክ አቀረበ፡፡

በመድረኩ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የሙዚቃ ትዕይንት እና የባህል አልባሳት ትዕይንት ተካሂዷል።

በመድረኩ የታደሙ የሴንትፒተርስበርግ ከተማ ነዋሪዎች በቀረበው የመድረክ ትዕይንት እንደተደሰቱ እና ስለኢትዮጵያ ባህልና የሙዚቃ ስልት እንደተረዱ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያን በዓለም መድረኮች በጥበብ የመግለጥ ተልዕኮን ያነገበው ኪን-ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በቻይና ትዕይንቱን ማቅረቡ አይዘነጋም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.