Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።

‎”በህብረት ችለናል ” በሚል መርህ በተካሄደው መድረክ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የህብረት ተምሳሌት እና የጽናት ምልክት ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ አንድነታችንን በማጠናከር በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮችም በጋራ መቆም ይኖርብናል ብለዋል።

የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የላብ፣ የደም እና የእንባ ውጤት መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ናቸው።

ለድጋፍ ሰልፍ የወጡ የከተማዋ ነዋሪች የህብረት ስፖርት ሰርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.